Fana: At a Speed of Life!

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በተገኙበት በጂቡቲ ዶልፊን አደባባይ ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ ተካሄዷል።
በቀጣናው ተምሳሌታዊ የምጣኔ ሃብት ግንኙነት ያላቸው ጂቡቲ እና ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትም ሰፊ ሥራዎችን በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቀደም ብሎ የጂቡቲ ከንቲባ እና ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በተገኙበት ከተተከሉት የካስያ ዝርያ ያላቸው ችግኞች መካከል መፅደቅ ያልቻሉትን በመተካት እና አዳዲስ የችግኝ ቦታዎችን በማዘጋጀት የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ነው የተባለው።
በሁለት ዙር ከ100 ሺህ በላይ ችግኞችን ለጂቡቲ ማስረከብ የተቻለ ሲሆን÷ የጂቡቲ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ተጨማሪ 40 ሺህ ችግኞች ወደ አገሪቱ እንደሚላክም ተመላክቷል፡፡
መንግሥት የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስኬታማ ልምዱን ከአገር ቤት በተጨማሪ ወደ ጎረቤት አገራት በማስፋት አረንጓዴ-ተኮር ቀጣናዊ ትስስርን እውን ለማድረግ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.