Fana: At a Speed of Life!

ጋምቤላ ክልል ከ966 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ላከ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ966 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላኩን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጅ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ወይዘሮ አኳታ ቻም÷ ለብሔራዊ ባንክ የተላከው ወርቅ በክልሉ ዲማ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ እና መንጌሽ ወረዳዎች ባሉ ባህላዊ ወርቅ አውጪዎች የተመረተ ነው።
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ብልጫ እንዳለው ጠቁመው÷ ይህም ምርቱ በኮንትሮባንድ ንግድ እንዳይባክን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የሚደረገውን ቁጥጥር በማጠናከር በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 600 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.