17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የበላይነት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡
በጂግጂጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
በውድድሩ÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን÷ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
ኦሮሚያ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ ኢኮስኮ እና ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በቅደምተከተላቸው ከ3ኛ እስከ 6ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በፍፃሜ ውድድሩ 11 ቡድኖች እና 3 ክልሎች በጠቅላላው 84 አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን÷ ለአሸናፊዎች የማበረታቻ ገንዘብና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል መባሉን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!