የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ ነው- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የልማት ጥያቄዎች ትኩረት የሚሹ ተግባራት በመሆናቸው የአሠራር ማዕቀፍን ተከትሎ ለመፍታት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እና የርዕሰ መስተደድር ፅሕፈት ቤት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን እና የቀሪ ወራት ዕቅድን ከዞን አስተዳደር ጋር እየገመገመ ነዉ፡፡
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤትና የርዕሰ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረሰ ገቲሳ ÷ በየደረጃው ከሕዝብ የሚነሱ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የአሠራር ማዕቀፉን ተከትሎ መፈጸምና ሌላውን መደገፍ ትኩረት የሚሹ ተግባራት መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው÷ በሁሉም የሥራ መስክ ዕቅድ አቅዶ በመምራት ተግባራትን በየወቅቱ እየገመገሙ ሥራዎችን ማሳለጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የሁሉም ዞኖች አስተዳደር የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የቀሪ ወራት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!