Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስትሮች እና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በቡልጋና ደብረ ብርሃን የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስትሮች እና የክልል  ርዕሳነ መስተዳድሮች በአማራ ክልል በቡልጋ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች የሚገኙ ነባር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝቱ  የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራል እና የክልልች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

 

በደብረ ብርሃን ከተማ 80 ቢሊየን ብርካፒታል አስመዝግበው ቦታ የተሰጣቸው 330 ነባር ኢንደስትሪዎች መኖራውን እና ከእነዚህ ውስጥ 52ቱ ኢንደስትሪዎች ሥራ ጀምረው ለ20 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ከደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ በዚህ ዓመት በአዲስ ኢንቨስት ለማድረግ ከቀረቡት 110 ፕሮጀክቶች ውስጥ 16 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ 50 ፕሮጀክቶች አዲስ ፈቃድ መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሕይወት ገልፀዋል።

በከተማው ያሉት ነባር ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ ለ70 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ሲሆን በአዲስ የተፈቀዱት ፕሮጀክቶች ደግሞ ለ20 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራለክ ተብሏል፡፡

በዘላለም ገበየሁ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.