ለውኃ እና ለአፈር አያያዝ አሠራሮቻችን ትኩረት ሰጥተን መሥራት አስፈላጊ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
የአረንጓዴዐሻራ መርኃ ግብር አንዱ ዓላማው የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ፣የግብርናን ምርታማነት ማሻሻል ፣ በረሀማነትና መዘዞቹን መከላከል እና ግድቦችን በደለል ከመሞላት መታደግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም በአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርን በስኬታማነት ለማስቀረት መቻሉን አንስተዋል፡፡
እንዲሁም በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያን ልምላሜ የማልበሱ ስራ ይቀጥላል ሲሉም መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡