Fana: At a Speed of Life!

በ9 ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የወጪንግድ 390 ሚሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9 ወራት ውስጥ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የወጪ ንግድ 390 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለፁ፡፡
ይህም የዕቅዱን 87 በመቶ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ አበረታች እድገት እያሳየ መሆኑን ያወሱት አቶ መላኩ የግብዓት ችግር፣ የመሰረተ ልማት እጥረት፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል ውስንነት፣ የፋይናንስና መሰል ችግሮች የዘርፉ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ለችግሮቹ ዕልባት ለመስጠትም በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
በአምስት ክልሎች ብቻ 396 ኢንዱስትሪዎች በተጠቀሱትና መሰል ችግሮች ምክንያት ስራ አቁመዋል ያሉት ሚኒስትሩ እነዚህን ወደስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪው ለሃገር ዕድገት ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ጠቁመው አዳዲስ ኢንቨስትመንትን መሳብና ነባር ኢንቨስትመንቶችን መደገፍ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ሀገሪቱ ያቋቋመቻቸው የኢንዱስትሪ ፖርኮች አልባሳትን ጨምሮ የተለያዩ ያለቀላቸው ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ናቸው።
በዘላለም ገበየሁ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.