Fana: At a Speed of Life!

በምርት ዘመኑ ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለተጠቃሚዎች ይቀርባል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር በ2014/15 ምርት ዘመን ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ አስታወቀ።
በዚህ ዓመት 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙ የተጠቆመ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየን ኩንታሉ እስካሁን ወደ አገር ውስጥ መግባቱ ተገልጿል።
የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሳ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት፥ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ግዥ መፈጸሙን ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑ 19 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ፍላጎት መኖሩን ጠቁመው በምርት ዘመኑ ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
እስካሁን ያልገባውና በተደጋጋሚ ጨረታ የወጣው ከፍተኛ መጠን ያለው የዩሪያ ማዳበሪያም ጂቡቱ ወደብ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ሳምንት ወደ አገር ቤት መግባት ይጀምራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ያብባል አዲስ በበኩላቸው፥ እስካሁን 4 ሚሊየን ኩንታል ከወደብ ወደ አገር ቤት እየተጓጓዘ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ በርካታ መጠን ያለው የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ መድረሱን ጠቁመው፥ ማዳበሪያውን ወደ አገር ውስጥ ለማጓጓዝ በቂ ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመጠው የፀጥታ ችግር፣ በአውራጅ እና ጫኝ በኩል የተፈጠረ የተጋነነ ዋጋ፣ ሕገ-ወጥ ኬላዎች፣ መጋዘን ላይ በፍጥነት ያለማራገፍ ችግሮች አጋጥመዋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.