Fana: At a Speed of Life!

የእሁድ ገበያ የዋጋ ንረት በማረጋጋት እና የኑሮ ጫና በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የእሁድ ገበያ ወደ 50 ቦታዎች ላይ መስፋፋቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቀ።
ከንቲባዋ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እና በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ያለባቸውን የኑሮ ጫና በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና እየተወጣ ይገኛል” ብለዋል፡፡
አቅርቦቱን በመጨመርና በማስፋት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲቀርብ በትኩረት ሰጥተን እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በየክፍለከተማው የእሁድ ገበያ እንዲስፋፋና እንዲለመድ ላስተባበሩ፣ ለመሩ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና አቅራቢዎች ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.