Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አውደ ርዕይና ባዛር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አውደ ርዕይና ባዛር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ዛሬ መካሄድ በጀመረው አውደ ርዕይና ባዛር 181 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ፣ 10 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ስምንት ተቋማት እየተሳተፍ ይገኛሉ፡፡
እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በሚቆየው አውደ ርዕይና ባዛር 22 ሺህ በሚሆኑ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አውደ ርዕይና ባዛሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርቶችና አገልግሎቶቻቸው በጥራትና ስብጥር የደረሱበትን ደረጃ ለተጠቃሚው ማሳወቅና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ያስችላልም ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራትና ስብጥር ያላቸው ምርቶችና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
አውደ ርዕይና ባዛሩን የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራና የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር በከር ሻሌ ናቸው ፡፡
በኤፍሬም ምትኩ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.