Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ481 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ481 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና ከ33 ሺህ በላይ ዩሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

በዛሬው ዕለት መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ መዳረሻውን ጅቡቲ ያደረገ 481 ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር እና 33 ሺህ 510 ዩሮ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

የምስራቅ ቀጠና ወንጀል ምርመራ ክላስተር ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ለሜሳ መኮንን እንደተናገሩት፥ መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገው ስካኒያ የጭነት መኪና ጋቢና ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘቡን ይዞ በመጓዝ ላይ ሳለ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ድሬደዋ ሦስት ኪሎ አካባቢ ልዩ ስሙ ገነት መናፈሻ በሚባለው ስፈራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ባደረጉት ጠንካራ ክትትልና ፍተሻ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ኃላፊው አያይዘውም መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ጠቁመው፥ እንደዚህ አይነት ወንጀሎች እየተበራከቱ መምጣታቸውንና የፀጥታው የጋራ ግብረ ኃይል በጋራ በመሆን መሰል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር በጋራ እየሰራ መሆኑን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.