Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በሰሜናዊ ኢራቅ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቱርክ በሰሜናዊ ኢራቅ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡

የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት እንደገለጸው የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) ታጣቂዎች ላይ ያነጣጥረ ድንበር ተሻጋሪ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሁሉሲ አካር እንደገለፁት ወታደራዊ ዘመቻው ጄቶችን፣ ሄሊኮፕተሮችን እና ድሮኖችን በመጠቀም በኮማንዶ ወታደሮች የምድር ላይ ውጊያም ይደረጋል ብለዋል፡፡
እስካሁን በተካሄደ ዘመቻ ቱርክ በሰሜን ኢራቅ ድንበር አካባቢ የሚገኙትን ሜቲና ፣ ዛፕ እና አቫሺን-ባሲያን የተባሉ የፒኬኬ ታጣቂዎች ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሁም ምሽጎችን እና የጥይት መጋዝኖችን በተሳካ ሁኔታ ማውደሟን መከላከያ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡
የቱርክ ጦር እያካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ በሲቪል ሰዎች እና በቅርሶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እያደረጉ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
መቀመጫውን በሰሜን ኢራቅ ያደረገው ፒኬኬ ነፃ የኩርድ ግዛትን ለመመስረት ከፈረንጆቹ 1984 ጀምሮ ወደ ሽምቅ ውጊያ መግባቱ ይነገራል።
ፓርቲው አሜሪካን ጨምሮ በብሪታንያ እና አውሮፓ ህብረት በአሸባሪነት መፈረጂን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.