Fana: At a Speed of Life!

የ33ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ በጌዴዮ ዞን ገርባሀሬ ወረዳ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ33ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች የምግብ ፍጆታዎች ድጋፍ አደረገ።

በደቡባዊ ሶማሊያ “ሴክተር 3 የአፍሪካ ኅብረት ሠላም አስከባሪ” ሥር ሆኖ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የ33ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ÷ የረመዳንን ፆምን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች የምግብ ፍጆታዎችን ድጋፍ አድርጓል።

በጌዴዮ ዞን ገርባሀሬ ወረዳ አስተዳደር ለሚገኙ ሼሆች ድጋፉን ያስረከቡት የሻለቃው እደላ ክፍል ኃላፊ ሻለቃ ቡሎ ነገራ እንደተናገሩት ÷ ሠራዊታችን በሄደበት ሁሉ ያለውን አካፍሎ በመኖር የሚታወቅ ነው።

እኛም ከዕለታዊ የምግብ ፍጆታችን ቀንሰን ለወገኖቻችን ያካፈልነው ያለንን ህዝባዊ ወገናዊነት ለማስቀጠል ነው።

የገርባሃሬ ወረዳ አስተዳደር አቶ ሀሰን ሼህ ኤልሚ በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሠላማችንን ከማስጠበቅ ባለፈ ችግሮቻችንን ተካፍሎ የሚኖር ታማኝ ህዝባዊ ሰራዊት ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ የረመዳንን ፆም በማስመልከት ለወገኖቻችን ላደረገው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ የወረዳው አስተዳደር ማመስገናቸውንም ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.