Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው – ዶክተር ቀነአ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ያለሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሕብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ ተናገሩ፡፡
ቢሮው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ለሕዝባዊ ሰራዊት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ÷ ያለሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሕብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ በበኩላው÷ የመዲናዋን ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሕዝባዊ ሰራዊቱ የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር የሚያደርገውን አስተዋጽኦ በዘላቂነት ለማስቀጠል ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.