Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ440 በላይ ደረሰ

ከአዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ከጥቂት ቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 443 መድረሱ ተገለጸ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ክዋዙሉ-ናታል ግዛት ከጥቂት ቀናት በፊት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተውን የጎርፍ እና የአፈር መደርመስ አደጋን ተከትሎ ሁለት የፖሊስ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ጨምሮ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 443 የደረሰ ሲሆን በአደጋው ምክንያት እስካሁን የጠፉ 63 ሰዎችም እየተፈለጉ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በጎርፍ አደጋው በርካታ ሆስፒታሎች እና ከ500 በላይ ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ተመላክቷል፡፡

ከዓለም አየር ንብረት ቀውስ ጋር በተያያዘ የአካባቢ ሙቀት እየጨመረ በመምጣቱ ጎርፍ እና ሌሎች መሰል ከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በከፍተኛ ሁኔታ እና በተደጋጋሚ እየተፈጠሩ በመሆናቸው የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ የዘርፉ ሳይንቲስቶች ማስጠንቀቃቸውን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.