Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋን ነዋሪዎች የሰላምና ፀጥታ ችግር ጥያቄ ለመመለስ የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ የሰላምና ፀጥታ ችግር ጥያቄዎች ለመመለስ በቅርበት የሚከታተል ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ።
መንግሥት የህዝቡን ችግሮች ለመፍታት ከህዝብ ጋር ውይይት እንዲደረግ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት÷ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በውይይቱ ወቅት በሰላምና ፀጥታ ችግሮች ዙሪያ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል የጋራ ግብረሃይል ተቋቋሟል፡፡
ግብረ ሃይሉ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ ሲሆን÷ የጋራ ዕቅድ በማዉጣት ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የፀጥታና መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ፍሰሐ ጋረደው ገልፀዋል።
በማዕከል ደረጃ የተቋቋመው ይህ ግብረ ሃይል በየጊዜው የከተማውን የሰላምና የፀጥታ ችግሮች እየገመገመ አፈፃፀሙን ሪፖርት የሚያደርግና ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ምክረ ሃሳብ በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የጋራ ግብረ ኃይሉ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የአፈፃፀም ዝርዝር መርሃ ግብር ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.