የአገልግሎት መስመሮች ላይ ኔትወርክ እንዲቆራርጥ የሚያደርጉ አካላትን ማጋለጥ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኃላፊነት በጎደላቸው እና የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስቡ የህዝብ ንብረት የሆነውንና በርካታ ህብረተሰብ የሚጠቀምበትን ኔት ወርክ እየዘረፉ በአገልግሎት አሰጣጠጡ ላይ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ህብረተሰቡ ሊያጋልጣቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለፋና ብርድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ኃይል እንዳይቆራረጥ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡
አክለውም ኃላፊነት በጎደላቸው እና የግል ጥቅምን በማሰብ የህዝብ ንብረት የሆነውንና በርካታ ህብረተሰብ የሚጠቀምበትን ኔት ወርክ እየዘረፉ በአገልግሎት አሰጣጠጡ ላይ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ህብረተሰቡ ሊያጋልጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በዚህም ከፊታችን የሚከበሩ በዓላትን ከለላ በማድረግ ዝርፊያ እንዳይካሄድ ህብረተስቡ የተለመደ ጥበቃውን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች ከኤክስፖርት ከኢንዱስትሪ ውጭ የሆኑ ደበኞች ለበዓሉ እና ለዋዜማው ኃይላቸውን እንዲቆጥቡም አሳስበዋል።
በየአካባቢው ያሉ ደላሎች መስመር እንዲቆረጥ እና መብራት እንዲጠፋ በማድረግ ገንዘብ አዋጡ የሚሉትን እንዲሁም የተቋሙ ሰራተኛ በመምስል መብራት በተቆረጠ ጊዜ ገንዘብ አዋጡ የሚሉ አካላትን ህብረተሰቡ አጋልጦ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!