Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 244 የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2014 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ወደ ክልሉ ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ ጥያቄ ያቀረቡና 11 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 244 ባለሃብቶች ወደ ስራ መግባት የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው ከክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል ነው የተባለው፡፡

በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሠማራት ፈቃድ የተሰጣቸው እነዚህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች ማምረት ወይም አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ 14 ሺህ 977 ጊዜያዊ እና 7 ሺህ 466 ቋሚ በድምሩ ለ22 ሺህ 443 ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተመላክቷል፡፡

ባለሃብቶቹ ፈጥነው ወደ ስራ በመግባት ዜጎችን ተጠቀሚ ማድረግ እንዲችሉም የክልሉ መንግስት ከመሬት አቅርቦት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ መገለፁን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.