Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ጊዜን የምንሻገረው አንድም እንደ ባህላችን ያለንን በማካፈል፤ ሁለትም መከራና ችግሩን ከስሩ ነቅሎ የመጣል ትግሉን በመካፈል ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ጊዜን የምንሻገረው አንድም እንደ ባህላችን ያለንን በማካፈል፤ ሁለትም መከራና ችግሩን ከስሩ ነቅሎ የመጣል ትግሉን በመካፈል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስገነዘቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2012 ያስጀመሩትን የ‘ማዕድ ማጋራት’ አጠናክረው ማስቀጠላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይየትንሣኤ በዓልን እና የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ለዓቅመ ደካሞች በዛሬው ዕለት ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ጊዜን የምንሻገረው አንድም እንደ ባህላችን ያለንን በማካፈል፤ ሁለትም መከራና ችግሩን ከስሩ ነቅሎ የመጣል ትግሉን በመካፈል ነው ብለዋል።

ያለን ማካፈል የአጭር ጊዜ መፍትሔ ሲሆን፥ ትግሉን መካፈል በረዥም ጊዜ በጋራ ራዕይ የተሻለ ነገን የምንፈጥርበት መንገድ ነውም ብለዋል።

የዛሬው ማዕድ ማጋራት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መቀስቀስ ምክንያት የተጀመረው አስቸጋሪ ጊዜን ተደጋግፎ የማለፍ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ከሰዓት በአንድነት ፓርክ በተካሄደው የ ’እናጋራ’ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ÷ 200 ለሚሆኑ የተቸገሩ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና አዳጊ ሕፃናት አስፈላጊ መሠረታዊ የምግብ ዓይነቶችን አጋርተዋል።

ድጋፍ ከተደረጉት የምግብ ዓይነቶች መካከል÷  ስንዴ፣ ጤፍ፣ ዘይት፣ ስኳር እና መኮሮኒ የሚገኙበት ሲሆን÷ እነዚሁ ምግቦች ተለይተው የታወቁ ቤተሰቦችን ለአጭር ጊዜ ለመደገፍ የታለሙ መሆናቸውንም ነው ጽሕፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ለእነዚሁ ወገኖች ተመልሰው በጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሶችን በመጠቀም የጓሮ ግብርናን ለማበረታታት በጓሮ ሊለሙ የሚችሉ የቆስጣ እና የሰላጣ ዘር ሰጥተዋል።

በአልዓዛር ታደለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.