Fana: At a Speed of Life!

ሩስያ ላይ ማዕቀብ በመጣል ችግሩን ከማባባስ ይልቅ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ማክበር ይገባል – የሰርቢያው ፕሬዚዳንት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የእኛ ተግባር ሩስያ ላይ ማዕቀብ በመጣል ችግሩን ከማባባስ ይልቅ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት መሥራት እና ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ማክበር ነው” ሲሉ የሰርቢያው ፕሬዚዳንት ተናገሩ።
የሰርቪያው ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ “ፒንክ” ለተባለ የቴሌቪዝን ጣቢያ እንደተናገሩት፥ በሩስያ ላይ የሚጣለው ማዕቀብ ሰርቪያን እንደ ሀገር ከባድ ዋጋ ሊያስከፍላት ይችላል፡፡
የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት ሰርቢያ ላይ ቀላል የማይባል ተጽእኖ እንደሚፈጥር የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፥ “የእኛ ተግባር ሩስያ ላይ ማዕቀብ በመጣል ችግሩን ከማባባስ ይልቅ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት መሥራት እና ዓለማቀፍ መርሆዎችን ማክበር ነው” ብለዋል፡፡
ሩስያ ከ2001 እ.ኤ.አ ጀምሮ የሰርቪያን የግዛት አንድነትን ስትደግፍ የነበረች ሀገር መሆኗንም አንስተዋል፡፡
የህዝቦቿ ኑሮ በሩስያ ጋዝ እና ዘይት ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ የሚነገርላት ሰርቪያ በሩስያ-ዩክሬን ጦርነት በምታራምደው ገለልተኛ አቋም እና በሞስኮ ላይ ማዕቀብ ባለመጣሏ በምእራባዊያን እንደምትተች ዘገባው አስታውሷል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቀደም ብለው ከሩሲያ ልዑክ አሌክሳንደር ቦካን-ካርቼንኮ ጋር ተገናኝተው ሰርቢያ ከሩሲያ እና ከቻይና ጋር የቀድሞ ወዳጅነቷን እና አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አፅንዖት ሰጥተው መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡
ውይይታቸውም በኃይል አቅርቦት መስክ እና የሰርቢያ-ሩሲያን ግንኙነትን የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በጋዝ አቅርቦት፣ ዋጋ፣ መጠን እና ሌሎች ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ ውይይትም በቅርቡ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.