ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከ4 ሺህ በላይ ለሆኑ አባወራዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ ለሚገኙ 4 ሺህ 350 አባወራዎች ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
በድጋፍ መልክ ከተሰጡ ቁሳቁስ መካከል÷ የሶላር የእጅ ባትሪዎች፣ ጀሪካኖች፣ የማዕድ ቤት እቃዎች፣ ምንጣፍ እና መጠለያ ያሉ መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያዎች ይገኙበታል፡፡
ተቋሙ ባለፈው ሳምንት በሰጠው ድጋፍ የሉጎ፣ ሜቲ እና ጋዲሳ ኦዳ ቀበሌ ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!