Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ13 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፍጠራቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ13 ሺህ በላይ በሆኑ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ የገበያ ልማት መርኃ ግብሮች በመሳተፍ ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፍጠራቸውን የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለጸ።

የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው ዕለት በጦር ኃይሎች አደባባይ በይፋ ተከፍቷል።

የቢሮ የኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ እንዳሉት÷ ኢንተርፕራይዞች የአገር ውስጥ ምርቶችን በብዛት እንዲመረቱና እንዲቀርቡ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

የአገር ውስጥ አቅምን በማሳደግና የውጭ ጫናን ጭምር በመቋቋም ኢንተርፕራይዞች በምርት ጥራትና በብዛት ምርታቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ እንደሆነም ነው ያብራሩት።

በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ13 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ የልማት መርኃ ግብሮች በመሳተፍ ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።

ከ58 በላይ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ለመላክ መዘጋጀታቸውን አብራርተው አንቀሳቃሾችም ምርታቸውን በማስተዋወቅ፣ በመሸጥ እንዲሁም የገበያ ዕድሉን በመጠቀም ምርትና ምርታማነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል ረዲ በበኩላቸው÷ በኤግዚቢሽኑና ባዛሩ ላይ የፋብሪካና የግብርና ምርቶች በስፋት ለተጠቃሚው እንደሚደርስ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.