Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች የተዘጋጀ የጎዳና ላይ የጋራ አፍጥር በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሶማሌ ክልል ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የጎዳና ላይ የጋራ አፍጥር መርሐ ግብር በጅግጅጋ ከተማ በሚገኙ ትላልቅ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል።
የጋራ አፍጥር መርሐ ግብሩ ዳያስፖራዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡት የ “ከኢድ እስከ ኢድ” ጥሪ አካል ሲሆን÷ በጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የአፍጥር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
በአፍጥር መርሐ ግብሩ ላይ ከ600 በላይ ሰዎች የጋራ አፍጥር ያደረጉ ሲሆን÷ በዝግጅቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የክልሉ ጸጥታና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙባሽር ዲባድ ራጌ ተገኝተዋል።
አቶ ሙባሽር በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር÷ “ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪ”ን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ላደረጉት ጥረት በማመስገን፣ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.