Fana: At a Speed of Life!

በተደጋጋሚ ለሚነሱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለ ስምምነት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የቻይናው ቴቢያን ኤሌክትሪክ አፓራተስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ  በተደጋጋሚ ለሚነሱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያችል የታመነበት የጂ አይ ኤስ ስዊች ጊር የማዕቀፍ ግዢ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ ለተቋሙም ከፍተኛ የሆነ የጥገና ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ዕድል ይሰጣል ተብሏል።

ስምምነቱ ለሶስት ዓመታት የሚቆይ የ15 እና 33 ኪሎ ቮልት ጂ አይ ኤስ ስዊች ጊርስ የማዕቀፍ ግዥ እንደሆነ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
በትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን ጨምሮ÷ ተደጋጋሚ ብልሽት ሲያጋጥማቸው የቆዩትን የ15 እና 33 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያዎች በአዲስ የጂ አይ ኤስ ስዊች ጊር ለመቀየር ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ግዢ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሚፈፀም ሲሆን÷ በዚህም 18 ባለ 15 ኪሎ ቮልት እና 26 ባለ 33 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ ስዊች ጊር በአዲስ ጂ አይ ኤስ ስዊች ጊር ይተካል ተብሏል፡፡
የማዕቀፍ ስምምነቱ በሚቆይበት የሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ65 በላይ የ15 እና 33 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያዎች ስዊች ጊር በአዲስ ጂ አይ ኤስ ስዊች ጊር ለመቀየር ታስቧል፡፡
የግዥ ስምምነቱ ከ16 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ በጀት የተያዘለት ሲሆን÷ ፋይናንሱም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡
ስምምነቱ በተደጋጋሚ ለሚነሱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለ ሲሆን ለተቋሙም ከፍተኛ የሆነ የጥገና ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ዕድል ይሰጣል መባሉን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.