Fana: At a Speed of Life!

በሚሌ – ኮምቦልቻ – ወረታ መስመር ኮንቴነሮችን ማስተናገድ መጀመሩን የወረታ ወደብና ተርሚናል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚሌ – ኮምቦልቻ – ወረታ መስመር ኮንቴነሮችን ማስተናገድ መጀመሩን የወረታ ወደብና ተርሚናል ገለጸ፡፡
ወረታ ወደብና ተርሚናል በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አስመጭና ላኪዎች የተቀላጠፈ የደረቅ ወደብ አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡
የወደቡ ተጠቃሚዎች እንደገለጹት÷ ከጂቡቲ – ሞጆ – በአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳርና ሌሎች የሰሜን-ምዕራብ አካባቢዎች የሚጓጓዙ ቁሳቁስ አቋራጭ በሆነ መንገድ ከጂቡቲ -ሚሌ -ኮምቦልቻ -ወረታ ለማስገባት አስችሏል።
በተጨማሪም ይደርስ የነበረውን የጊዜና የገንዘብ ብክነት ቀንሷል።
የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ አያሌው ወደቡ ብዛት ያላቸው ኮንቴነሮች ማስተናገዱን ጠቅሰው፥ በ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግን በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት መንድ በመዘጋቱ 1 ሺህ 520 ኮንቴነሮችን ብቻ እንዳስተናገደ ተናግረዋል።
በወጪ ደረጃ ሲታይ አንድ ትልቅ ኮንቴነር ከጅቡቲ – ኮምቦልቻ – ወረታ ሲመጣ እስከ 60 ሺህ ብር ወጪ ሲኖረው ከጅቡቲ በአዲስ አበባ ወረታ ሲገባ ግን እስከ 200 ሺህ ብር ወጪ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ የተጠገነው የጨረቲ ወንዝ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት በመሆኑ ኮንቴነሮች በሚሌ – ኮምቦልቻ – ወረታ መምጣት መጀመሩን አመላክተዋል።
አሁን ላይ መንገዱ ክፍት መኾኑ ታውቆ አስመጭና ላኪዎች ወረታ ወደብና ተርሚናልን በመጠቀም የተለመደ ንግድና ኢንቨስትመንታቸውን ማስቀጠል እንደሚችሉ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.