Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ባለፉት 9 ወራት ለ340 ሺህ 638 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል-የከተማ አስተዳደሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ባለፉት 9 ወራት ለ340 ሺህ 638 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
 
አስተዳደሩ ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት÷ በተጠቀሰው ጊዜ ለ329 ሺህ 79 ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ 340 ሺህ 638 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም የእቅዱን 103 በመቶ ማሳካት መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
 
ከተፈጠረው የስራ እድል ውስጥ 92 በመቶው ቋሚ እና 8 በመቶው ጊዜያዊ መሆኑን የጠቆመው አስተዳደሩ÷ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ከቴክኒክና ሙያ ለተመረቁ 16 በመቶ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ጠቁሟል፡፡
 
አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ከማደራጀትና ህጋዊ ሰውነት ከመስጠት አንፃር 12 ሺህ 926 አንቀሳቃሾችን የያዙ 3 ሺህ 983 ኢንተርፕራይዞችን የማደራጀት ስራ መሰራቱም ተመላክቷል፡፡
 
የገበያ ትስስር አሠራርን በማዘመን ለ13 ሺህ 108 ኢንተርፕራይዞች 67 ሺህ 346 አንቀሳቃሾች 5 ቢሊየን 933 ሚሊየን 25 ሺህ 130 ብር መጠን ያለው የገበያ ትስስር መፍጠር ተችሏል ነው የተባለው፡፡
 
ከዚሁ ጋር በተያያዘ 29 አውደ ርዕይና ባዛሮችን በማዘጋጀት 2 ሺህ 785 ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ 53 ሚሊየን 110 ሺህ 225 ብር እንዲያገኙ መደረጉን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.