Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር ዘይት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ

በአዲስ አበባ፣ሚያዝያ 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል መጪዎቹን የፋሲካና የኢድ አልፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር ዘይት እየተሰራጨ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገልጿል፡፡

የቢሮው ሀላፊ አቶ ማሄ ቦዳ÷ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ የክልሉ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይ ቀናት የሚከበሩትን የፋሲካና የኢድ አልፈጥር በዓላትን በማስመልከትም 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሁሉም አካባቢዎች የማዳረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዘይት በተጨማሪ ስኳር ከተለያዩ አከፋፋዮች ጋር በመሆን እየተሰራጭ መሆኑን የገለፁት ሃላፊው የመጡ የፍጆታ እቃዎች በሸማች ማህበራት እና በቸርቻሪ ነጋዴዎች አማካኝነት እንደሚሰራጩም ገልፀዋል።

በመንግስት ድጎማ የመጡ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በህገ ወጦች እጅ እንዳይገባ ህብረተሰቡ ክትትል ማድረግ እንዳለበት አመላክተው ምርት ኖሮ የአቅርቦት እጥረት ከተከሰተም በአቅራቢያ ላሉ የሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ እንደሚገባ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.