Fana: At a Speed of Life!

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለተፈናቃሉ ወገኖች በዓል መዋያ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ለበዓል መዋያ ከ870 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የእርድ ከብቶችን ድጋፍ አድርገዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት÷ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ለማድረግ በመጡበት ጊዜ ዳግም ተመልሰው የቻሉትን እገዛ ለማድረግ ቃል በገቡት መሰረት ለሁለቱም እምነት ተከታዮች የበዓል መዋያ የሚሆኑ የእርድ ከብቶችን ይዘው መምጣታቸውን ገልጸዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ በጦርነቱ አቅሙ በመዳከሙ ብዙ ማገዝ ባይችልም የስደትን አስከፊነት በተግባር ስለሚረዳ በመፈናቀላችሁ ሀዘኑ ከፍ ያለ ነው ያሉት ሊቀ ጳጳሱ÷ ሀገራችን በፈተና ወድቃ፣ የዜጎች መፈናቀል እና ሰቆቃ እንዲያበቃ እና መልካም ጊዜ እንዲመጣ ሁሉ በየእምነቱ ጸንቶ መጸለይና ይህን የፈተና ጊዜ ማለፍ የሚቻልበትን በጎ ሥራ ማከናወን እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ተፈናቃዮቹ በበኩላቸው÷ በቤተ ክርስቲያኗና በእሳቸው በኩል እየተደረገላቸው ስላለው ድጋፍማመስገናቸውን ከደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ከ34 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ የዞኑ ምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.