Fana: At a Speed of Life!

ሃብትን በቁጠባ መጠቀም የሚያስችል የበጀት ወጪ አስተዳደር ስርዓት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃብትን በቁጠባ መጠቀም የሚያስችል የበጀት ወጪ አስተዳደር ስርዓት እንደሚያስፈልግ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር በከር ሻሌ ገለጹ፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፋይናንስና በጀት አስተዳደር አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ፥ በማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ዶክተር በከር ሻሌ በመድረኩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ፥ እንደ አገር የተደረገው ተቋማዊ የአደረጃጀት ለውጥ ወጪን የሚቀንስና ውጤታማ የሥራ ፍሰት እንዲኖር ታሳቢ ያደረገ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመሆኑም ዓለም አቀፍ ጫናዎችን እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን መቋቋምና ሀብትን በቁጠባ መጠቀም የሚያስችል የበጀት ወጪ አስተዳደር ስርዓት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፥ የፋይናንስና በጀት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችም የተቀመጡ የበጀት ታሳቢዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለቀጣይ ዓመት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ከሥራ ጋር የተመጠነ የመዋቅር ትግበራ፣ በትንሽ ወጪ ውጤታማ ሥራን መሥራት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን መጠቀም፣ አላስፈላጊ ወጪን ማስወገድ፣ የፕሮጀክት አስተዳደርን ማሻሻል፣ ብክነትንና ሙስናን መፀየፍ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.