Fana: At a Speed of Life!

በአውደ ውጊያዎች የሠራዊቱን አባላት ላገለገሉ የህክምና ባለሙያዎችና ተቋማት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለያየ አውደ-ውጊያዎች ላይ የተጎዱ የሠራዊት አባላትን ላገለገሉ የህክምና ባለሙያዎች እና ተቋማት እውቅና ሰጠ።

በመርሃ-ግብሩ የመከላከያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቢሾፍቱ ሆስፒታል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተገኝ ለታ ÷ የተለያዩ የህክምና ተቋማትና ባለሙያዎች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት ህክምና መስጠታቸውን ተናግረዋል።

በሙያቸው የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ እንዲሁም አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ እገዛዎችን ላደረጉ አካላት እውቅና መሰጠቱን ገልጸዋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በበኩላቸው÷ የአንድን ሀገር ህልውና ለማስጠበቅ እና ሰራዊቱን ለማጠናከር የህዝብ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አመላክተው የጤና ተቋማትና ሙያተኞች የሕዝብ ደጀንነታቸውን በተግባር ማረጋገጣቸውን አንስተዋል።

እውቅና ከተሰጣቸው የህክምና ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷዓለም ደነቀ÷ የህክምና ባለሙያዎች ባለፈው ተከስቶ በነበረው ጦርነት የተጎዱ ወታደሮችን በማከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

እንደ ባለሙያ ሀገሪቱ ከእነሱ የምትፈልገውን ማንኛውንም ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.