Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የኔዘርላንድስ እና የቤልጂዬም ዲፕሎማቶችን አባረረች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ 15 የኔዘርላንድስ እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የቤልጂዬም ዲፕሎማቶችን አባረረች፡፡
 
ዲፕሎማቶቹ በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ ሩሲያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
እርምጃው በኄግና በአምስተርዳም በሚገኙ የሩሲያ ኤምባሲዎች፣ የዓለም አቀፍ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ክልከላ ድርጅት እና በሌሎች የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሩሲያ ተወካዮች እና ሰራተኞች መባረራቸውን ተከትሎ የተደረገ የአጸፋ ምላሽ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ኔዘርላንድስ እንደ ዓለም አቀፍ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ክልከላ ድርጅት መቀመጫ አገርነቷ መብቶቿን አላግባብ መጠቀም አልነበረባትም ሲል ድርጊቱን ኮንኗል፡፡
 
በፈረንጆቹ 1997 ዓለም አቀፍ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች ክልከላ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ስምምነትን በጥብቅ ማክበር አለባትም ብሏል ሚኒስቴሩ።
 
ሚኒስቴሩ በመግለጫው የቤልጂዬም ዲፕሎማቶች እስከ ቀጣዩ ግንቦት 3 ቀን ድረስ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ እንደተናገራቸው ማሳወቁንም አናዶሉ ዘግቧል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.