Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ሲቀበሉ የተገኙ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር የግንባታ ቤትን ምክንያት በማድረግ ያለ አግባብ ገንዘብ ሲቀበሉ የተገኙ ሁለት የደንብ ቁጥጥር ባለሙያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ እንደገለፁት ባለሙያወቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው ግንባታ የሚያከናውኑ ግለሰብን ፈቃድ የሌላቸው በማስመሰልና እናስፈርሳለን በማለት ገንዘብ እንዲከፍሉ በማስገደድ ግለሰቡ ለፀጥታ አካላት በሰጡት ጥቆማ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ህገ-ወጦችን ለመከላከል አስተዳደሩ በሚሰራው ስራዎች በባለቤትነት በመያዝ እና የእጅ መንሻን በመቃወም ለክፍለ ከተማው ሰላም መስፈን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ህገ-ወጥ ተግባራትን በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ ማቅረባቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.