Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያዘጋጀው የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ስነስርዓት አካሂዷል።
 
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ÷ ረመዳንን ፈጣሪ በሚያዘው መሠረት በጋራ እና በአንድነት ልናሳልፍ ይገባል ብለዋል።
 
ያለው ለሌለው በማካፈል የቆየ የመረዳዳት ባህላችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሠው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ከኢድ እስከ ኢድ አገራዊ ጥሪን ተቀበለው ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን አየር መንገዱ 20 በመቶ ቅናሽ አድርጓል ።
 
አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ አገራት ደንበኞቹ በሀጂ እና ኡምራ ጉዞ የቆየ ደንበኝነት ያለው መሆኑን አስታውሰዋል::
 
በቀጣይም የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በኢፍጣር ስነ ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ፣ የአየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች፣ የእስልምና እምነቱ ታላላቅ አባቶችና ተከታዮች እንዲሁም የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.