በጅማ ከተማ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ ጾሙን እየጾሙ ያሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና አቅመ ደካሞች ተሳትፈዋል።
መርሐ ግብሩን በጅማ ከተማ የሚገኙ የአብሮነት፣ ራሂሙን እና ኑሩልሙታጅ የተሰኙ የመረዳጃና የበጎ አድራጎት ማህበራት ናቸው ያዘጋጁት፡፡
የከተማዋ የእስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ ሼህ መሃመዳሚን ተማም ኢፍጣሩን በቁጥባ አስጀምረው የመግሪብ ሶላት በጋራ ተሰግዷል።
ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማፍጠር እና እርስ በርስ መረዳዳት እውነተኛ የእስልምና አስተምህሮ መሆኑን ኡስታስ ሼህ ሙሃመዳሚን አውስተዋል፡፡
የተቀደሰውን ታላቁን የረመዳን ጾም አንደበትን ከክፉ ቃል እና ምግባር ቆጥቦ በእስላማዊ ስነ ምግባር እርስ በርስ በመረዳዳት ማሳለፍ ይገባልም ብለዋል።
ወርቅአፈራው ያለው