የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡
የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሙ በዘጠኝ ወረዳዎች በ67 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 35 ሺህ 350 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊ÷ የፕሮግራሙ መጀመር በምግብ እጥረት ምክንያት የሚታየውን የተማሪዎች ማቋረጥና የመድገም ምጣኔን ለመቀነስ እና ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመሳብ እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የፕሮግራሙ መጀመር 600 ለሚሆኑ ወገኖች የስራ ዕድልን እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
በምንያህል መለሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!