Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ አሪዞና ግዛት የተከሰተው የሰደድ እሳት ከ700 በላይ ቤቶችን አወደመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሰሜናዊ አሪዞና ገጠራማ አካባቢ በተነሳ ንፋስ የተከሰተው የሰደድ እሳት ከ700 በላይ ቤቶችን ማውደሙ ተገለጸ።

በሰሜናዊ አሪዞና ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፍላግስታፍ ከተማ ወጣ ብሎ የተነሳው ፈጣን ሰደድ እሳት ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን እና ይህን ተከትሎም በአካባቢው የአደጋ ጊዜ መታወጁ ተመላክቷል።

የሰደድ እሳቱ ከ23 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ የሸፈነ ሲሆን ቢያንስ 24 ህንፃዎች ማውደሙ ተገልጿል።

አደጋው በተከሰተበት ሰሜናዊ አሪዞና ፍላግስታፍ ከተማ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን 766 ቤቶች ወድመዋል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ከ1 ሺህ በላይ እንስሳት አካባቢውን ለቀው መሸሻቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል።

እሳቱ አሁንም ድረስ በአስጊ ሁኔታ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ የጣለ ሲሆን ተጨማሪ ውድመት እንዳያስከትልም ተሰግቷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.