Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ የገጠሙ ግለሰቦች ከነተባበሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል በለገጣፎ ለገ ዳዲ ከተማ 01 ቀበሌ በተለመዶ ገዋሳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ የገጠሙ ግለሰቦች ከነተባበሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከለገጣፎ ለገዳዲ ፖሊስ መምሪያ ጋር ባደረጉት የቅንጅት ሥራ እስካሁን ከተቋሙ እውቅና እና አሰራሩ ውጭ ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መንገድ የተገጠሙ 70 ቆጣሪዎች እና ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው 15 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአካባቢው ምሰሶዎችን ጨምሮ በማይታወቁ ግለሰቦች የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ገመዶች እንዲሁም ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን÷ በአንድ ግለሰብ ቤት የተጠቀለለና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረትነት የሚጠረጠር የኤሌክትሪክ ገመድ ተገኝቷል፡፡

በሕገ ወጥ ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ቆጣሪ በሚገጥሙበት ወቅት ከተገጠመላቸው ግለሰቦች ከእያንዳንዳቸው ከ20 እስከ 35 ሺህ ብር እንደተቀበሉ የግል ተበዳዮች ተናግረዋል፡፡

የለገጣፎ ለገዳዲ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ወርቁ በዳኔ÷ በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉና በመሰል ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን በቀጣይ ከክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ይደረጋል ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፊንፊኔ ዙሪያ ዲስትሪክት የሕግ ክፍል ኃላፊ አቶ የኋላእሸት አብረሃም÷ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ በሕገ ወጥ መንገድ አገልግሎት እንሰጣለን በሚል የተቋሙ ሰራተኛ በመምሰል የሚሰማሩ ግለሰቦችን የፀጥታ አካላት፣ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት እና ህብረተሰቡ በሕገ ወጥ ተግባር ላይ የሚሰማሩ ግለሰቦችን በመከላከል ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.