Fana: At a Speed of Life!

በወልድያ ከተማ የተቀበረ የታንክ ቅምቡላ ፈንድቶ የአካልና የንብረት ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልድያ ከተማ መልካ ቆሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጥር የተቀበረ የታንክ ቅምቡላ ፈንድቶ የአካል ጉዳት ማድረሱን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ቅምቡላው የፈነዳው በሰው ሲነካካ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ በአንድ ሰው ላይ የአካል እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።
የፖሊስ መምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ተመስገን ቢረሳው በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባት ወጣት ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል መላኳን ተናግረዋል።
የታንክ ቅምቡላው በአካባቢው በነበሩ ሶስት ኮንቲነሮችና በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት እንዳደረሰ መናገራቸውን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.