የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር የክፍያ መተግበሪያ ከኢትዮጽያ አየር መንገድ ጋር ለመስራት ተስማማ

By Meseret Awoke

April 20, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር የክፍያ መተግበሪያ በኩል የአየር መንገዱ ደንበኞች የትኬት ክፍያ መፈጸም የሚያስችለውን ስምምነት አድርገዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በስምምነቱ ወቅት “ሁለቱ አንጋፋ ተቋማት ያደረጉት ስምምነት እንደ ሀገር የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማሳለጥ የተጀመረውን ጉዞ የሚያፋጥን ይሆናል” ብለዋል።

የቴሌ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር በአጭር ጊዜ ውስጥ እየጨመረ የመጣ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!