Fana: At a Speed of Life!

አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ደብቆ ለማዘዋወር ሞክሯል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ግለሰቡ በቁጥር 107 ፍሬ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር በዝግጅት ላይ እያለ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

እፁን ወደ አማራ ክልል ጎንደር አካባቢ ለመውሰድ እቅድ የነበረው ግለሰብ በየካ ክፍለ ከተማ ላምበረት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መያዙን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.