የሀገር ውስጥ ዜና

አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Feven Bishaw

April 20, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ደብቆ ለማዘዋወር ሞክሯል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ግለሰቡ በቁጥር 107 ፍሬ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር በዝግጅት ላይ እያለ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡