Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 215 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአምራቹ ለማድረስ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመኽር ወቅት ልማት የሚውል 215 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአምራቹ እየተሰራጨ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የግብርና ግብአትና የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሽራ ሲሳይ እንዳመለከቱት÷ በክልሉ ለመኸር ወቅት 300 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ከተለያዩ አካላት ለማሰብሰብ ታቅዷል።

ከዚህ ውስጥ 215 ሺህ ኩንታል በመሰብሰብ የማሰራጨት ስራ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀው ከተሰበሰበው የምርጥ ዘር ውስጥም 104 ሺህ ኩንታል የሚሆነው የበቆሎ ምርጥ ዘር፤ ቀሪው የስንዴ፣ ጤፍና ሌሎች የሰብል ዝርያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 1ሺህ 800 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ጠቁመው÷ ዘሩ ያልደረሳቸው አርሶ አደሮች በአቅራቢያቸው ካሉ የህብረት ስራ ማህበራት መውሰድ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

አርሶ አደሩ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመውም ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የህብረት ስራ ማህበራትም የሚያደርጉትን ስርጭቱን ፍትሃዊ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

በ2014/2015 ዓ.ም የመኸር ወቅት በክልሉ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያየ የሰብል ዘር በመሸፈን 143 ሚሊየን ኩንታል ለማግኘት መታቀዱን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.