Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የጦር መኮንኖች በወቅታዊ ሁኔታ ገለፃ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል የኢትዮጵያን ሁኔታ በሚመለከት ከአምስት የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የጦር መኮንኖች ገለፃ አደረጉ።

የጦር መኮንኖቹ በታንዛኒያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ስልጠና እየተከታተሉ ያሉ ሲሆን ፥ ከናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ ፣ ቡሩንዲ ፣ ዚምባብዌና ሩዋንዳ የተውጣጡ ናቸው።

ለቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና አሁናዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ ያደረጉት አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ፥ ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናት የተሻገረ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ታሪክ እንዳለት አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለ ብዙ ወገን መድረኮች ያላትን ተሳትፎም አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ እየደረሰባት ያለውን ኢ-ፍትሃዊ ጫና በሚመለከት ለጦር መኮንኖቹ አባላት ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደሩ ፥ የሁላችንም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ በመሆኑ ይህን ድርጊት ለመቃወም አፍሪካውያን በህብረት መቆም አለብን ብለዋል።

ከአባይ ውሃ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ ውሃውን ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ባካተተ መልኩ በፍትሃዊነትና ምክንያታዊነት የመጠቀም ፅኑ አቋም እንዳላት አስረድተዋል።

አምባሳደር ፍስሃ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማንኛውንም የተፋሰሱ ሀገራት የማይጎዳ የልማት አጀንዳ ነው መሆኑንም አመላክተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላትም የተደረገላቸውን ገለፃ አድንቀው ፥ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ በደሎች በሁሉም የአፍራካ ሀገራት ላይ የተደቀነ ጫና በመሆኑ ልንተባበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የዓባይ ውሃ ጉዳይም የተፈሰሱ ሀገራት ጉዳይ በመሆኑ መታየት ያለበት በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስራ ብቻ ነው ብለዋል።

የጦር መኮንኖቹ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር መስራት በሚችሉት የትብብር ጉዳዮች ላይም ከአምባሳደር ፍስሃ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.