Fana: At a Speed of Life!

ፋብሪካዎች ለሚቀጥሉት 3 ወራት ጥሬ ቆዳና ሌጦን እርድ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች በቀጥታ እንዲገዙ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ጥሬ ቆዳና ሌጦን እርድ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች በቀጥታ መሰብሰብ እንዲችሉ መፈቀዱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፉን ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ ቁጥር 814/2006 መሰረት ግዢ ለመፈጸም እና ከእርድ እስከ ፋብሪካ ባለው ግብይት ሰንሰለት ምርቶቹ እየተጎዱ እና ከደረጃ በታች እየሆኑ ነው የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ከጥሬ ቆዳና ሌጦ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ማግኘት ካለመቻሏ ባለፈ ምርቶቹን በአግባቡ ሰብስቦ ፋብሪካዎች ጋር በተፈለገው ጥራት መጠን ማድረስ አለመቻሉ ተመላክቷል፡፡

ማህበረሰቡ በእርድ ወቅት የሚያገኘውን ጥሬ ቆዳ የሚገዛው አጥቶ ለአገር በርካታ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችለውን ሃብት በየአካባቢው ለመጣል መገደዱም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ፋብሪካዎቹ በቀጥታ ከአራጆች መግዛት እንዲችሉ ባቀረቡት ጥያቄ መነሻነትም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጊዜው እርድ የሚፈጸምበት መሆኑን ታሳቢ አድርጎ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት መጠየቁን አመላክቷል፡፡

ስለሆነም የተፈጠውን ችግር ለመቅረፍ ከዛሬ ጀምሮ ላሉት ሶስት ተከታታይ ወራት የቆዳ ፋብሪካዎች ጥሬ ቆዳ እና ሌጦን እርድ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች በቀጥታ መግዛት እንዲችሉ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.