የሀገር ውስጥ ዜና

ፋብሪካዎች ለሚቀጥሉት 3 ወራት ጥሬ ቆዳና ሌጦን እርድ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች በቀጥታ እንዲገዙ ተፈቀደ

By Feven Bishaw

April 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ጥሬ ቆዳና ሌጦን እርድ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች በቀጥታ መሰብሰብ እንዲችሉ መፈቀዱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፉን ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ ቁጥር 814/2006 መሰረት ግዢ ለመፈጸም እና ከእርድ እስከ ፋብሪካ ባለው ግብይት ሰንሰለት ምርቶቹ እየተጎዱ እና ከደረጃ በታች እየሆኑ ነው የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ጠቁሟል፡፡