Fana: At a Speed of Life!

የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የድርቅ ምላሽ ኮሚቴ መደበኛ ጉባኤ የተካሄደ ሲሆን ÷ በመድረኩ የድርቁ ምላሽ ሁኔታና መጣል የጀመረውን የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች መንግስት የጀመረውን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ሥራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፤ የዝናብ ወቅት በመሆኑ ዝናቡ ሊያስከትል ከሚችለው አደጋ አስመልክቶ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እንደሚገባ እና ከወዲሁ የተጀመረውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ መሆኑን ከስምምነት መደረሱን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.