የሀገር ውስጥ ዜና

የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ

By Feven Bishaw

April 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የድርቅ ምላሽ ኮሚቴ መደበኛ ጉባኤ የተካሄደ ሲሆን ÷ በመድረኩ የድርቁ ምላሽ ሁኔታና መጣል የጀመረውን የበልግ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቋቋም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።