Fana: At a Speed of Life!

አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ከ100 በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ከ100 በላይ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን የጎፋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።
የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዝታ አብርሃም÷ ሕዝብን ለማማረር ምርት በመጋዘን የደበቁ፣ በመንግሥት ድጎማ የሚቀርቡ ምርቶችን በሕገ ወጥ ሁኔታ የሸጡ እንዲሁም ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ሲሸጡ በተያዙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡
በዓልን ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በሥራ ላይ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
ከዶሮ ጀምሮ ለበዓል የሚሆኑ የተለያዩ ምርቶችን አርሶ አደሩ ያለ ደላላ ጣልቃ ገብነት በቀጥታ ወደ ገበያ በማቅረብ እየሸጡ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ሲያጋጥመው ህብረተሰቡ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲያደርግ ኃላፊዋ አሳስበዋል፡፡
በማቴዎስ ፈለቀ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.