የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን ፖሊስ አስታወቀ

By Melaku Gedif

April 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትንሳኤ በዓል ጋር ተያይዞ በገበያና በሌሎች ሥፍራዎች ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ÷ በተለይም የሕዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ በመዝናኛ ሥፍራዎች ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ አስፈላጊው ክትትልና ጥበቃ እንደሚደረግ ነው የገለጹት።

በበዓላት ወቅት በርካታ ግዥና ሽያጭ ስለሚካሄድ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች በገበያው ሊሰራጩ ስለሚችሉ ኅብረተሰቡ እንዳይታለል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠይቀው ኅብረተሰቡም አጠራጣሪ የብር ኖት ሲመለከትም ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

ኅብረተሰቡም የከተማዋ ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ይህንን ድጋፍ ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውንም አጠራጣሪ የወንጀል ድርጊቶች ሲመለከት በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 011-1- 11-01-11 እንዲሁም 991 ነጻ የስልክ ጥሪ በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጥም አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!