Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 998 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 998 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ከተመላሾች መካከል ወንድ 708፣ ሴት 272 እና 18 ህጻናት ሲሆኑ ፥ ተመላሾች አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.